Diaspora news
የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ሳምንት በመጪዉ ጥር ይከበራል
የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ማህበር በመጪዉ ጥር ወር ለማዘጋጀት ስላሰበዉ ትልቅ ድግስ በቤልቪዉ ሆቴል የተለያዩ ሚዲያዎች በተገኙበት መግለጫ የሰጠ ሲሆን ይህም ኤቨንት የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ሳምንት የሚባልና በዉስጡም እንደ ኤግዚብሽን፤ ሲንፖዚየም ፤ የእራት ግብዣ እና ግሬት ዲያስፖራ ሩጫ ያካተተ ትልቅ ፕሮግራም ነዉ፡፡ ይህም ፕሮግራም በኢትዮጵያ አዲስ አበባ እና በካናዳ ቶሮንቶ የሚደረግ ሲሆን በዚሁም ፕሮግራም ዲያስፖራዉን ከሀገሩ ጋር ያለዉን ግንኙነት የበለጠ እንዲያጠብቅ ብሎም በኢንቨስትመንት በኢኮኖሚና በተለያዩ ዘርፎች ላይ በሀገሩ ላይ ያለዉን ተሳትፎ እንዲጨምር የሚያበረታታ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ይህም ኤቨንት የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ሳምንት የሚባልና በዉስጡም እንደ ኤግዚብሽን፤ ሲንፖዚየም ፤ የእራት ግብዣ እና ግሬት ዲያስፖራ ሩጫ ያካተተ ትልቅ ፕሮግራም ነዉ፡፡ ይህም ፕሮግራም በኢትዮጵያ አዲስ አበባ እና በካናዳ ቶሮንቶ የሚደረግ ሲሆን


ይህንንም ፕሮግራም የሀገራችን አርማ የሆነዉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአንደኛ ደረጃ እስፖንሰር ያደረገ ሲሆን አንጋፋዉ ዳሽን ባንክ እና እናት ባንክም እስፖንሰር በማድረግ ተሳትፈዋል በዚሁ አጋጣሚ የሚዲያ አጋራችንን አርትስ ቲቪን እያመሰገንን በመጪዉ ጥር ለሚዘጋጀዉ ታላቅ የዲያስፖራ ሳምንት ሁሉንም ዲያስፖራ እንዳትቀሩ ለመጋበዝ እንወዳለን፡፡
Write a Comment
Search Here
comment